30. በየዕለቱም እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጠዋት ጠዋት ይቆሙ ነበር፤ ይህንንም ማታ ማታ
31. እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ ይፈጽሙ ነበር፤ በተወሰነላቸው ቊጥርና በተሰጠውም መመሪያ መሠረት ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።
32. ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኛው ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኀላፊነት ያከናውኑ ነበር።