2. እንዲሁም መላውን የእስራኤልን መሪዎች፣ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።
3. ዕድሜያቸው ሠላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ቊጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ።
4. ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺህ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ይቈጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺህ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤
5. አራቱ ሺህ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራቱ ሺህ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔርን ያመስግኑ”።
6. ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀዓትና በሜራሪ በየጐሣቸው መደባቸው።
7. ከጌድሶናውያን ወገን፤ለአዳን፣ ሰሜኢ።
8. የለአዳን ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
9. የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤ሰሎሚት፣ ሐዝኤል፣ ሐራን፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።እነዚህ የለአዳን ቤተ ሰብ አለቆች ናቸው።