1 ዜና መዋዕል 2:7-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የከርሚ ወንድ ልጅ አካን፤እርሱም ፈጽሞ መደምሰስ የነበረበትን ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።

8. የኤታን ወንድ ልጅ፤አዛርያ።

9. የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።

10. አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤

11. ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ።

12. ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ።

13. የእሴይ ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣

14. አራተኛ ልጁ ናትናኤል፣ አምስተኛ ልጁ ራዳይ፣

15. ስድስተኛ ልጁ አሳም፣ ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።

16. እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣኤል ነበሩ።

17. አቢግያ አሜሳይን ወለደች፤ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።

18. የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ ከዓዙባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ያሳር፣ ሶባብ፣ አርዶን።

19. ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።

20. ሆር ኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።

21. ከዚያም በኋላ ኤስሮም ሥልሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።

22. ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር።

1 ዜና መዋዕል 2