1 ዜና መዋዕል 2:45-52 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

45. ሸማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ።

46. የካሌብ ቁባት ዔፉ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።

47. የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።

48. የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደችለት።

49. እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።

50. እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ።የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤ሦባል የቂርያትይዓሪም አባት፤

51. ሰልሞን የቤተ ልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።

52. የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኵሌታ፣ ሀሮኤ፤

1 ዜና መዋዕል 2