44. ሽማዕ ረሐምን ወለደ፤ ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ። ሬቄም ሸማይን ወለደ፤
45. ሸማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ።
46. የካሌብ ቁባት ዔፉ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።
47. የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።
48. የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደችለት።
49. እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።
50. እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ።የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤ሦባል የቂርያትይዓሪም አባት፤
51. ሰልሞን የቤተ ልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።
52. የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኵሌታ፣ ሀሮኤ፤
53. እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጐሣዎች፤ ይትራውያን፣ ፉታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፣ ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ከእነዚህ የመጡ ጐሣዎች ነበሩ።
54. የሰልሞን ዘሮች፤ቤተ ልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኵሌታ፣ ጾርዓውያን።
55. በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጐሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።