2. ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ አሴር።
3. የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።
4. የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም ባጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
5. የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ኤስሮም፣ ሐሙል።
6. የዛራ ወንዶች ልጆች፤ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፤ ባጠቃላይ አምስት ናቸው።
7. የከርሚ ወንድ ልጅ አካን፤እርሱም ፈጽሞ መደምሰስ የነበረበትን ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።
8. የኤታን ወንድ ልጅ፤አዛርያ።
9. የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።
10. አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤
11. ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ።
12. ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ።
13. የእሴይ ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣