1 ዜና መዋዕል 17:25-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. “አምላኬ ሆይ፤ ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጸህለታል፤ ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት አገኘ።

26. እግዚአብሔር ሆይ፤ በእውነት አንተ አምላክ ነህ፤ ይህንንም መልካም ተስፋ ለባሪያህ ሰጥተሃል።

27. በፊትህ ለዘላለም እንዲኖር አሁንም የባሪያህን ቤት ልትባርክ ወደሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የባረክኸው አንተ ስለ ሆንህ፣ ለዘላለም የተባረከ ይሆናል።”

1 ዜና መዋዕል 17