1 ዜና መዋዕል 17:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፣ ነቢዩ ናታንን “እነሆ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።

2. ናታንም ለዳዊት፣ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ፣ ያሰብከውን ሁሉ አድርግ” ሲል መለሰለት።

1 ዜና መዋዕል 17