1 ዜና መዋዕል 16:16-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣ለይስሐቅ የማለውን መሐላ።

17. ይህንንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤

18. እንዲህ ሲል፣ “የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ።”

19. ቍጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፣በእርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፣

20. ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ፣ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ።

1 ዜና መዋዕል 16