1 ዜና መዋዕል 15:4-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የአሮንን ዘሮችና ሌዋውያኑንም በአንድነት ሰበሰበ፤

5. ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤

6. ከሜራሪ ዘሮች፣አለቃውን ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤

7. ከጌድሶን ዘሮች፣አለቃውን ኢዮኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤

8. ከኤሊጻፋን ዘሮች፣አለቃውን ሸማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤

9. ከኬብሮን ዘሮች፣አለቃውን ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹን፤

10. ከዑዝኤል ዘሮች፣አለቃውን አሚናዳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።

11. ከዚያም ዳዊት ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፣ ሌዋውያኑን ኡርኤልን፣ ዓሣያን፣ ኢዩኤልን፣ ሸማያን፣ ኤሊኤልንና አሚናዳብን ጠርቶ፣

12. እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ እናንተ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ስለ ሆናችሁ፣ እናንተና ወንድሞቻችሁ ሌዋውያን ራሳችሁን ቀድሱ፤ ከዚያም የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀሁለት ቦታ አምጡ።

13. የአምላካችን የእግዚአብሔር ቍጣ በላያችን ላይ እንዲህ የነደደው እናንተ ሌዋውያኑ ቀድሞም ስላላመጣችሁት ነው፤ እኛም ብንሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በታዘዘው መሠረት አልጠየቅነውም።”

1 ዜና መዋዕል 15