24. ካህናቱ ሰበኒያ፣ ኢዮሣፍጥ፣ ናትናኤል፣ ዓማሣይ፣ ዘካርያስ፣ በናያስና አልዓዛር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። ዖቤድኤዶምና ይሒያ ደግሞ የታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ።
25. ስለዚህ ዳዊት የእስራኤል ሽማግሌዎችና የሻለቃው አዛዦች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።
26. የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን እግዚአብሔር ረድቶአቸው ስለ ነበር፣ ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች ሠዉ።