1 ዜና መዋዕል 14:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. በዚያ ሳለ የወለዳቸው የልጆቹ ስም ይህ ነው፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፣

5. ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣

6. ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣

7. ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት።

8. ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ተቀብቶ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኀይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ይህን ሰምቶ ስለ ነበር ሊገጥማቸው ወጣ።

9. በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን መጥተው የራፋይምን ሸለቆ ወረሩ።

10. ስለዚህ ዳዊት፣ “ወጥቼ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልን? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” ብሎ መለሰለት።

1 ዜና መዋዕል 14