1 ዜና መዋዕል 14:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና አናጢዎችን ከዝግባ ዕንጨት ጋር ላከ።

2. ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ አንግሦ እንዳጸናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግሥቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት አስተዋለ።

3. ዳዊትም በኢየሩሳሌም ብዙ ሚስቶች አገባ፤ ከእነርሱም ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

1 ዜና መዋዕል 14