1 ዜና መዋዕል 12:30-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ከኤፍሬም ሰዎች በጐሣዎቻቸው ዘንድ ታዋቂ የሆኑ ብርቱ ተዋጊዎች ሃያ ሺህ ስምንት መቶ፤

31. ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች፤ እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በየስማቸው ተጽፈው የመጡ ነበሩ።

32. ዘመኑን የተረዱና እስራኤላውያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤ በእነርሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው።

33. ልምድ ያላቸው፣ በሁሉም ዐይነት መሣሪያ ለመዋጋት የተዘጋጁና ዳዊትን ለመርዳት የመጡት መንታ ልብ የሌላቸው የዛብሎን ሰዎች ሃምሳ ሺህ፤

34. ከንፍታሌም ሰዎች አንድ ሺህ የጦር አለቆች፤ ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የያዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ሰዎች፤

35. ከዳን ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ሃያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ፤

1 ዜና መዋዕል 12