1 ዜና መዋዕል 11:24-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. የዮዳሄ ልጅ በናያስ የፈጸመው ጀብዱ ይህ ነበር፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ዝነኛ ሆነ።

25. ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ ክብር ተጐናጸፈ፤ ይሁን እንጂ ክሦስቱ አንዱ አልነበረም፤ ዳዊትም የክብር ዘቡ አዣዥ አደረገው።

26. ኀያላኑም እነዚህ ነበሩ፤የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣የቤተ ልሔሙ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

1 ዜና መዋዕል 11