20. የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ።
21. ከሦስቱ አንዱ ሆኖ ባይቈጠርም እንኳ፣ እጥፍ ክብር አገኘ፤ አዛዣቸውም ሆነ።
22. ከቀብስኤል የመጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠራው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ። እርሱም እጅግ የታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎችን ገደለ። እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሸፈነበት ቀን ወደ አንድ ጒድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።
23. ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብፃዊ ገደለ፤ ግብፃዊው የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር በእጁ ቢይዝም፣ በናያስ ግን ቆመጥ ይዞ ገጠመው፤ ከግብፃዊው እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
24. የዮዳሄ ልጅ በናያስ የፈጸመው ጀብዱ ይህ ነበር፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ዝነኛ ሆነ።
25. ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ ክብር ተጐናጸፈ፤ ይሁን እንጂ ክሦስቱ አንዱ አልነበረም፤ ዳዊትም የክብር ዘቡ አዣዥ አደረገው።
26. ኀያላኑም እነዚህ ነበሩ፤የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣የቤተ ልሔሙ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣
27. ሃሮራዊው ሳሞት፣ፊሎናዊው ሴሌድ፣
28. የቴቊሔ ሰው የሆነው የዒስካ ልጅ፣ዒራስ፣ የዓናቶቱ ሰው አቢዔዜር፣
29. ኩሳታዊው ሴቤካይ፣አሆሃዊው ዔላይ፣
30. ነጦፋዊው ማህራይ፣የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣
31. ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታይ፣ጲርዓቶናዊው በናያስ፣
32. የገዓስ ሸለቆዎች ሰው የሆነው ኡሪ፣ዓረባዊው አቢኤል፣
33. ባሕሩማዊው ዓዝሞት፣ሰዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣
34. የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፣የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣
35. የሃራራዊው የሳኮር ልጅ አሒአም፣የኡር ልጅ ኤሊፋል፣
36. ምኬራታዊው ኦፌር፣ፍሎናዊው አኪያ፣
37. ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፤
38. የናታን ወንድም ኢዮኤል፣የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፣