1 ዜና መዋዕል 10:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. በሸለቆው ውስጥ የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ ሰራዊቱ እንደ ሸሸ፣ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ከተሞቹን ያዙ።

8. በማግሥቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ ሲመጡ፣ ሳኦልና ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።

9. ሳኦልን ከገፈፉ፣ ራሱን ከቈረጡና መሣሪያውንም ከወሰዱ በኋላ፣ ለአማልክቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲነግሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክተኞችን ላኩ።

10. ከዚያም መሣሪያውን በአማልክቶቻቸው ቤተ ጣዖት አኖሩ፤ ራሱንም በዳጎን ቤተ ጣዖት ውስጥ አንጠለጠሉት።

1 ዜና መዋዕል 10