1. ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን መውጋት ጀመሩ፤ እስራኤላውያንም ከፊታቸው ሸሹ፤ ብዙዎች በጊልቦዓ ተራራ ላይ ሞቱ።
2. ፍልስጥኤማውያን ሳኦልንና ልጆቹን ይበልጥ አሳደዱአቸው፤ የሳኦልንም ልጆች ዮናታንን፣ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሉ፤
3. ሳኦል በተሰለ ፈበት ግንባር ውጊያው በረታ፤ ቀስተኞችም አግኝተው አቈሰሉት።
4. ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን፣ “እነዚህ ሸለፈታሞች መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ” አለው።ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር አልደፈረም፤ ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።