1 ዜና መዋዕል 1:41-52 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. የዓና ወንድ ልጅ፤ዲሶን።የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን፣ ክራን።

42. የኤጽር ወንዶች ልጆች፤ቢልሐን፣ ዛዕዋን፣ ዓቃን።የዲሳን ወንዶች ልጆች፤ዑፅ፣ አራን።

43. በእስራኤል አንድም ንጉሥ ገና ሳይነግሥ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ ከተማዪቱም ዲንሃባ ትባል ነበር።

44. ባላቅ ሲሞትም የባሶራ ሰው የሆነው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

45. ኢዮባብ ሲሞት የቴማን አገር ሰው የሆነው ሑሳም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

46. ሑሳም ሲሞት በሞዓብ ምድር ምድያምን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። የከተማዪቱም ስም ዓዊት ተባለ።

47. ሃዳድም ሲሞት የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

48. ሠምላም ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለችው የረሚቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

49. ሳኡልም ሲሞት የዓክቦር ልጅ የሆነው በኣልሐናንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

50. በኣልሐናን ሲሞት ሀዳድ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። ከተማውም ፋዑ ትባል ነበር፤ ሚስቱ መሄጣብኤል ትባላለች፤ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።

51. ሀዳድም ሞተ። ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣

52. አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣

1 ዜና መዋዕል 1