1 ዜና መዋዕል 1:11-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ምጽራይም የሉዲማውያን፣ የዐናማውያን፣ የላህባማውያን፣ የነፍተሂማውያን፣

12. የፈትሩሲማውያን፣ የፍልስጥኤማውያን ቅድመ አባቶች የሆኑት የከስሉሂ ማውያንና የከፍቶሪማውያን ነገዶች አባት ነው።

13. ከነዓን የበኵር ልጁ የሆነው የሲዶን እንዲሁም የኬጢያውያን፣

14. የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣

15. የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣

16. የአራዴዎያውያን፣ የሰማርያውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነው።

17. የሴም ወንዶች ልጆች፤ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም።የአራም ወንዶች ልጆች፤ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ።

18. አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ሳላም ዔቦርን ወለደ።

19. ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤በዘመኑ ምድር ስለተከፈለች፣ የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተብሎ ተጠራ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

20. ዮቅጣንም፡አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣

21. ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣

22. ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣

23. ኦፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው።

1 ዜና መዋዕል 1