1 ነገሥት 9:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ይሁን እንጂ ኪራም ከጢሮስ ተነሥቶ ሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ለማየት በሄደ ጊዜ አልተደሰተባቸውም፤

13. እርሱም፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ ከተሞች ምንድን ናቸው?” አለ፤ እነዚህንም ‘ከቡል ምድር’ አላቸው፤ እስከ ዛሬም በዚሁ ስም ይጠራሉ።

14. በዚያን ጊዜ ኪራም ለንጉሡ መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ልኮለት ነበር።

1 ነገሥት 9