1 ተሰሎንቄ 5:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እናንተ ግን፣ ወንድሞች ሆይ፤ ይህ ቀን እንደ ሌባ ያስደነግጣችሁ ዘንድ በጨለማ ውስጥ አይደላችሁም፤

5. ሁላችሁም የብርሃን ልጆች፣ የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ ወገን አይደለንም፤

6. እንግዲህ እንንቃ፤ ራሳችንንም እንግዛ እንጂ እንደሚያንቀላፉት እንደ ሌሎቹ አንሁን።

7. የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉ፤ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና።

1 ተሰሎንቄ 5