1 ተሰሎንቄ 3:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ በጭንቀታችንና በመከራችን ሁሉ በእምነታችሁ ምክንያት በእናንተ ተጽናናን።

8. በጌታ ጸንታችሁ ስለ ቆማችሁ በርግጥ አሁን በሕይወት እንኖራለን።

9. በእናንተ ምክንያት በአምላካችን ፊት ስላገኘነው ደስታ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምን ያህል ምስጋና ልናቀርብ እንችላለን?

10. እንደ ገና ልናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለማሟላት ሌሊትና ቀን እጅግ ተግተን እንጸልያለን።

11. አሁንም ራሱ አምላካችንና አባታችን፣ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅናልን።

1 ተሰሎንቄ 3