1 ቆሮንቶስ 7:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ጻፋችሁልኝ ጒዳይ፣ ሰው ወደ ሴት ባይደርስ መልካም ነው፤

2. ነገር ግን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት።

3. ባል ለሚስቱ የሚገባትን ሁሉ ያድርግላት፤ ሚስትም እንዲሁ ለባሏ የሚገባውን ሁሉ ታድርግለት።

4. ሚስት አካሏ የራሷ ብቻ አይደለም፤ የባሏም ነው፤ እንዲሁም ባል አካሉ የራሱ ብቻ አይደለም፣ የሚስቱም ነው።

1 ቆሮንቶስ 7