1 ቆሮንቶስ 5:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በመካከላችሁ የዝሙት ርኵሰት እንዳለ በርግጥ ይወራል፤ እንዲህ ያለው ርኵሰት በአረማውያን ዘንድ እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ነው፤ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለና።

2. ደግሞም ታብያችኋል! ይልቅስ ሐዘን ተሰምቶአችሁ፣ ይህን ድርጊት የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ልታስወግዱት አይገባምን?

1 ቆሮንቶስ 5