1 ቆሮንቶስ 1:19-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፤“የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤የዐዋቂዎችንም ዕውቀት ከንቱ አደርጋለሁ።”

20. ጠቢብ የት አለ? ሊቅስ የት አለ? የዘመኑስ ፈላስፋ የት አለ? እግዚአብሔር የዓለምን ጥበብ ሞኝነት አላደረገምን?

21. ከእግዚአብሔር ጥበብ የተነሣ ዓለም በገዛ ጥበቧ እግዚአብሔርን ማወቅ ስለ ተሳናት፣ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ያድን ዘንድ የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአል።

1 ቆሮንቶስ 1