1. ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ፣ ልጆቹን ፈራጆች አድርጎ በእስራኤል ላይ ሾማቸው።
2. የበኵር ልጁ ኢዮኤል ሲሆን፣ ሁለተኛው ልጁ አብያ ነበረ፤ እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር።
3. ነገር ግን ልጆቹ የአባታቸውን ፈለግ አልተከተሉም፤ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከመንገዱ ወጡ፤ ጒቦ ተቀበሉ፤ ፍርድም አጣመሙ።
4. ስለዚህ የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው ሳሙኤል ወዳለበት ወደ አርማቴም መጡ።