1 ሳሙኤል 28:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. እርሱም፣ “አልበላም” በማለት እምቢ አለ።ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትዮዋ ጋር ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ፤ ከመሬትም ተነሥቶ በዐልጋ ላይ ተቀመጠ።

24. ሴትዮዋም በቤቷ የሠባ ጥጃ ስለነበራት፣ፈጥና ዐረደችው፤ ዱቄት ወስዳ ለወሰች፣ እርሾ የሌለው እንጀራም ጋገረች።

25. ከዚያም ለሳኦልና ለሰዎቹ አቀረበችላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ በዚያም ሌሊት ተነሥተው ሄዱ።

1 ሳሙኤል 28