1 ሳሙኤል 27:11-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጎአል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጌት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ፣ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።

12. አንኩስም በልቡ፣ “እርሱ ራሱ የገዛ ሕዝቡ የሆኑት እስራኤላውያን እጅግ እንዲጠሉት ስላደረገ፣ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል” ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።

1 ሳሙኤል 27