1 ሳሙኤል 23:27-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፣ “ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወረውታልና ቶሎ ድረስ!” አለው።

28. ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፣ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያን ቦታ ስም “የመለያያ ዐለት” ብለው ጠሩት።

29. ዳዊትም ከዚያ ወደ ላይ ወጥቶ በዐይንጋዲ ምሽጎች ተቀመጠ።

1 ሳሙኤል 23