1 ሳሙኤል 2:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ምስኪኑንም ከጒድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ከመኳንንቱ ጋር ያስቀምጣቸዋል፤የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል።“የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፣ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጎአል።

9. እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል፤ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ፤“ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤

10. ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ፤እርሱ ከሰማይ ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል።“ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”

11. ከዚያ በኋላ ሕልቃና ወደ ቤቱ ወደ ራማ ሄደ፤ ብላቴናው ግን በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።

1 ሳሙኤል 2