1 ሳሙኤል 15:22-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤“ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፣ እግዚአብሔር፣በሚቃጠል ቍርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን?እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።

23. ዐመፅ እንደ ጥንቈላ ያለ ኀጢአት፣እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው። አንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቅህ፣ እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”

24. ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና የአንተን መመሪያ ጥሻለሁ፤ ሕዝቡን ፈርቼ ስለ ነበር፣ የጠየቁኝን ታዝዣለሁ።

1 ሳሙኤል 15